የሰኞ ማለዳ የሰራተኞች የዕውቀት ሽግግር መርሀ ግብር ተካሄደ፡፡

by | ዜና

(ህዳር 23/2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የሰኞ ማለዳ ከስራ ሰዓት መግቢያ በፊት የሚያዘጋጀው የሰራተኞች የዕውቀት ሽግግር መርሀ ግብር የተካሄደ ሲሆን በመድረኩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ፣ የቢሮ ማኔጅመንት አባላትና ሰራተኞች ተሳታፊ ሆነዋል።

                       
በመርሀ ግብሩ ላይ የአፋን ኦሮም ስርዓተ ትምህርት ዳሬክተር አቶ ተሾመ ቀናሳ የጃፓን የትምህርት ልምድን የሚገልጽ ሰነድ ያቀረቡ ሲሆን በመድረኩ ማጠቃለያ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ልምዶችን በመቅሰም ለላቀ ስራ መትጋት ለትምህርት ልማት ስራው ውጤታማነት ከፍተኛ አበርክት እንዳለው አመላክተዋል፡፡

                         

0 Comments