(ህዳር 19/2017 ዓ.ም) ቀኑ ዘንድሮ በአለም አቀፍ ደረጃ ለ21ኛ እንዲሁም በሀገራችን ለ20ኛ ጊዜ “ወጣቶችን ማዕከል ያደረገ የጸረ ሙስና ትግል የነገን ሥብዕና ይገነባል” በሚል መሪ ቃል እንደሚከበር የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የስነምግባርና ፀረ ሙስና መከታተያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አስራት ሽፈራው በፌደራል ስነምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን የተዘጋጀ የመወያያ ሰነድ ባቀረቡበት ወቅት አስታውቀዋል።
የትምህርት ሴክተሩ በስነ ምግባር የታነጸ ትውልድ ለመፍጠር ያስቀመጠው ተልዕኮ የሚፈለገውን ውጤት ማስመዝገብ እንዲችል አለም አቀፉ የፀረ ሙስና ቀን የሚከበርበትን አላማ በተመለከተ በየትምህርት መዋቅሩ ለሚገኙ የትምህርት ማህበረሰቦች በቂ ግንዛቤ መፍጠር እንደሚገባ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ አሊ ከማል አመላክተዋል።
ሙስናም ሆነ ብልሹ አሰራር የሀገርን እድገት የሚገታ ተግባር ከመሆኑ ባሻገር ህዝብ በህግ የበላይነት ላይ አመኔታ እንዳይኖረው የሚያደርግ ተግባር እንደመሆኑ የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ለግል ጥቅማቸው የሚያውሉ አካላትን ተጠያቂ የማድረግ ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ወንድሙ ኡመር ጠቁመው የቢሮው ሰራተኞችም እለቱን አስመልክቶ የተላለፉ መልዕክቶችን መሰረት በማድረግ የተጣለባቸውን ኃላፊነት በአግባቡ ሊወጡ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
የመርሀ ግብሩ ተሳታፊዎች በቀረበው የመወያያ ሰነድ መሰረት ሙስናና ብልሹ አሰራር የሀገር ኢኮኖሚ በሚፈለገው ደረጃ እድገት እንዳያ ሳይም ሆነ የስነምግባር ቀውስ እንዲባባስ የሚያደርግ ችግር በመሆኑ ሙስናን እና ብልሹ አሰራርን ለመከላከል የተደነገጉ የህግ ማዕቀፎች ተግባራዊ እንዲሆኑ ሁሉም የሚጠበቅበትን ኃላፊነት ሊወጣ እንደሚገባ አስረድተዋል።
0 Comments