(ህዳር 13/2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሰራተኞች የብልፅግና ፓርቲን የአምስት ዓመታት የምስረታ በዓልን ምክንያት በማድረግ በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት የተዘጋጀውን ኤግዚቪሽን ጎብኝተዋል።
በጉብኝቱ ላይ በከተማ አስተዳደሩ ባለፉት አምስት አመታት የተከናወኑ አንኳር ስራዎች በቪአር ፣ በቪዲዮ ፣ በፍቶና በምዴሎች ቀርበው ገለፃ የተሰጠባቸው ሲሆን በጉብኝቱ ወቅት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ፣ የቢሮው ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ ወንድሙ ዑመር እና ሌሎች አመራሮች ተገኝተዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሰራተኞች በትላንትናው እለት ተመርቆ የተከፈተውን ኤግዚቪሽን ጎበኙ።
0 Comments