የሰው ሀብት ልማትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ለቢሮው ሰራተኞች የመንግስት ሰራተኞች አስተዳደር አዋጅ ቁ.56/2010ን ጨምሮ በተለያዩ ደንቦች እና መመሪያዎች ዙሪያ ለሁለተኛ ዙር ስልጣኞች ስልጠና መስጠት ጀመረ።

by | ዜና

(ጥቅምት 27/2017 ዓ.ም) ስልጠናው ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ሲሆን ስልጠናው ለሁሉም የቢሮው ሰራተኞች በዙር እንደሚሰጥ በአዘጋጆች ተገልጿል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የሰው ሀብት ልማትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ስዩም በቀለ በስልጠናው መክፈቻ ባስተላለፉት መልዕክት ስልጠናው የቢሮው አጠቃላይ ሰራተኞች በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ሰራተኞች አስተዳደር አዋጅ ቁ.56/2010 እንዲሁም በሌሎች ተያያዥ መመሪያዎችና ደንቦች ዙሪያ በቂ ግንዛቤ ፈጥረው ውጤታማ ስራ መስራት እንዲችሉ ታስቦ መዘጋጀቱን አስታውቀዋል።

ዳይሬክተሩ አያይዘውም ከመንግስት ሰራተኞች አስተዳደር ጋር በተገናኘ የሚወጡ አዋጆችም ሆኑ ደንቦች የሰራተኞችን ዕውቀት በተገቢው ሁኔታ መጠቀም የሚያስችል የአሰራር ስርአት ለመዘርጋት ታስቦ እንደመሆኑ ስራ ክፍሉ በቀጣይ ተመ ሳሳይ ስልጠና መስጠቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አመላክተዋል። ስልጠናዉም በቀጣይ ዙር ለተቀሩ የቢሮ ሰራተኞች ተሰጥቶ የሚጠናቀቅ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ስልጠናው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ የህግ ባለሙያ በሆኑት አቶ በቃሉ ከበደ አማካይነት የተሰጠ ሲሆን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ሰራተኞች አስተዳደር አዋጅ ቁ.56/2010 የወጣው በከተማ ውስጥ እየተመዘገበ ያለውን እድገት ማስቀጠል የሚያስችል ፐብሊክ ሰርቪስ ለመፍጠር ታስቦ መሆኑን አቶ በቃሉ ጠቁመው ሰራተኞችም አዋጆቹንም ሆነ ደንቦችን በአግባቡ ተገንዝበው ኃላፊነታቸውን በአግባቡ መወጣት እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል።

0 Comments