(ጥቅምት 26/2017 ዓ.ም) በኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ፣ በአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ እና ኑፍ አፍሪካ ምርምርና ስልተጠና ተቋም ቅንጅት መምህራንን በ “Innovative Pedagogy” ለማብቃት ሲሰጥ የቆየው ዘርፈ ብዙ ተግባር ዛሬ ጥቅምት 26 ቀን 2017 ዓ.ም የተገመገመ ሲሆን፣ መምህራን ከዘመኑ እጅግ ፈጣን እና ተለዋዋጭ ቴክኖሎጂ ጋር ራሳቸውን እንዲያዋሕዱና ብቁ ሆነው እንዲገኙ ማስቻል የምርጫ ጉዳይ እንዳልሆነ የኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ዶ/ር ብርሃነመስቀል ጠና ገልጸዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ በበኩላቸው፣ ቢሮው በዚህ ረገድ ዕቅድ ይዞና ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መሆኑን ገልጸው፣ ዩኒቨርሲቲው ይህንን አጅግ አስፍቶና አጠንክሮ እንዲሄድበት አደራ ብለዋል።
በዚህ አዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ እና የአዲስ አበባ ትምህርት ጥራት እና ቁጥጥር ባለስልጣን በጋራ በመሆን በገመገሙበት መድረክ፣ ጊዜውን የሚመጥንና ዓለም የደረሰበትን የማስተማር ስነ ዘዴ በመጠቀም በማስተማር በትምህርት ጥራቱ ላይ ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል ከስምምነት ተደርሷል።
መምህራንን “Innovative Pedagogy” ብቁ የማድረጉ ተግባር መቀጠል እንዳለበት ተገለጸ።
0 Comments