(ጥቅምት 26/2017 ዓ.ም) ስልጠናው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የፈተ እና ምዘና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት አማካይነት ተዘጋጅቶ ለክፍለ ከተማ የፈተና ባለሙያዎች ፤የስርአተ ትምህርት ቡድን መሪዎች ፤ዘርፉን ለሚያስተባብሩ ስራ መሪዎች እንዲሁም ለቢሮው የስርአተ ትምህርት ባለሙያዎችና ሱፐርቫይዘሮች ነው የተሰጠው፡፡
ስራ ክፍሉ ፈተናዎችን ከማዘጋጀት እና ከማስተዳደር ባሻገር በየትምህርት እርከኑ የሚማሩ ተማሪዎች በትምህርታቸው ውጤታማ እንዲሆኑ የተለያዩ የጥናትና ምርምር ስራዎችንም ሆነ የመማር ብቃት ምዘናዎችን እንደሚያካሂድ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የፈተ እና ምዘና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዲናኦል ጫላ ጠቁመው የዛሬው መርሀግብርም በዝቅተኛ የክፍል ደረጃ የሚማሩ ተማሪዎችን የንባብ ክሂል ምዘና ለማካሄድ በሚያስፈልጉ መሳሪያዎች ዙሪያ ከሀገር አቀፍ የፈተናዎች ኤጀንሲ በመጡ ባለሙያዎች አማካይነት በቂ ግንዛቤ ለመፍጠር ታስቦ መሰጠቱን አስታውቀዋል፡፡
በዝቅተኛ የክፍል ደረጃ በተለይም የሁለተኛ እና ሶስተኛ ክፍል የሚማሩ ተማሪዎች የንባብ ክሂል ምዘና ለማካሄድ በሚያስፈልጉ ጉዳዮች ዙሪያ በቂ ግንዛቤ በመፍጠር በቀጣይ በክፍለከተማ ደረጃ ምዘና ለማካሄድ የሚያግዝ ስልጠና መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የመማር ብቃት ምዛና ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ብሩክ መንግስቱ ገልጸዋል፡፡
የዝቅተኛ ክፍል የንባብ ክሂል ምዘና መሳሪያዎች (EGRA TOOLS) ለማዘጋጀት በሚያስፈልጉ ጉዳዮች ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ፡፡
0 Comments