የአጠቃላይ ትምህርት ሱፐርቪዥን ዳይሬክቶሬት በአንደኛ ሩብ አመት በዘርፉ የተከናወኑ ተግባራት አፈጻጸምን ገመገመ።

by | ዜና


(ጥቅምት 15/2017 ዓ.ም) በመርሀ ግብሩ በየደረጃው የሚገኙ ሱፐርቫይዘሮች የተሳተፉ ሲሆን በተመረጡ የ1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ክላስተር ማዕከላት የአማርኛ እና የአፋን ኦሮሞ የሱፐርቪዥን ሪፖርት በተወካዮች ከመቅረቡ ባሻገር የቢሮው የአንደኛ ሩብ አመት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል።

በአንደኛ ሩብ አመት በትምህርት ቤቶች በተካሄደ የአጠቃላይ ትምህርት ሱፐርቪዥን ከዝግጅት ምዕራፍ ጀምሮ በየደረጃው የተከናወኑ ተግባራትን በመከታተል የተለያዩ ድጋፎች መደረጋቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ትምህርት ሱፐርቪዥን ቡድን መሪ ትግስት ድንቁ የሩብ አመቱን ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት ጠቁመው በክፍል ውስጥ በተደረገ የሱፐርቪዥን ስራ መምህራን አመታዊ፣ ሳምንታዊ እና እለታዊ እቅድ አዘጋጅተው ወደተግባር መግባታቸውን በማረጋገጥም ሆነ የክፍለ ጊዜ ብክነት መኖር አለመኖሩን በተመለከተ የድጋፍና ክትትል ስራ ከመሰራቱ ባሻገር ለሚመለከታቸው አካላት ግብረ መልስ መ ሰጠቱን አስታውቀዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ትምህርት ሱፐርቪዥን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አብዱልበር መሀመድ በዛሬው ውይይት በአንደኛ ሩብ አመት ከቢሮ ጀምሮ እስከ ትምህርት ቤት ድረስ በሱፐርቪዥን ዘርፍ የተከናወኑ ተግባራትን በመገምገም እና በሂደት የተስተዋሉ ችግሮችን በመቅረፍ በቀጣይ ውጤታማ የድጋፍና ክትትል ስራ ለመስራት እንደሚያስችል ጠቁመው ቢሮው በ2017 ዓ.ም ትኩረት ያደረገበት ተማሪዎችን በሒሳብና እንግሊዘኛ የትምህርት አይነቶች ውጤታማ የማድረግ ተግባር የተሳካ እንዲሆን ሱፐርቫይዘሮች በየትምህርት ቤቱ ተገቢውን የድጋፍና ክትትል ስራ መስራት እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል።

0 Comments