የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በደሞዝ ማስተካከያ አፈፃፀም መመሪያ ላይ በቢሮው ለሚገኙ ዳይሬክቶሬቶችና ለአዳሪ ትምህርት ቤቶች ኦረንቴሽን ሰጠ::

by | ዜና

(ጥቅምት 14/2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በደሞዝ ማስተካከያ አፈፃፀም መመሪያ ላይ የከተማ አስተዳደሩ ፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሀብት ልማት ቢሮ በሰጠው ኦረንቴሽን መሰረት በቢሮው መካሄድ ስላለበት ቅድመ ዝግጅትና በማስፈፀም ሂደት ውስጥ በሚጠበቁ ጉዳዮች ላይ በቢሮ ለሚገኙ ዳይሬክቶሬቶች እና ቡድን መሪዎች እንዲሁም ለእቴጉ መነን የሴት ተማሪዎች አዳሪ ትምህርትቤትና ለገላን የወንዶች አዳሪ ትምህርት ቤት አመራሮችና የሰው ሀብት ቡድን መሪዎች ኦረንቴሽን ተሰጥቷል::

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በደሞዝ ማስተካከያ አፈፃፀም መመሪያ መሰረት የሚፈለጉ መረጃዎችን በአግባቡ በማደራጀት በተቀመጠው ጊዜ ገደብ ውስጥ በማቅረብ ለአፈጻጸሙ መደላድል መፍጠር ተገቢ መሆኑን ገልጸዋል::

የቢሮ ኃላፊ አማካሪ ወ/ሮ አበበች ነጋሽ በበኩላቸው በከተማ አስተዳደሩ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ የተሰጡ አቅጣጫዎችን ተግባራዊ ለማድረግ የሚሰሩ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን አብራርተው ለአተገባበሩ ስኬታማነት ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ ጠይቀዋል ::

0 Comments