ለቢሮው የስርአተ ትምህርት ባለሙያዎች በኢ-ስኩል ሲስተም አተገባበር ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ፡፡

by | ዜና

(ጥቅምት 14/2017 ዓ.ም) ስልጠናው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ ልማትና ማስፋፋት ዳይሬክቶሬት እና ሲስተሙን ባለማው ትሪያ ትሬዲንግ በጋራ የተዘጋጀ ሲሆን በቢሮው የኢንፎረሜሽን ኮሚኒኬሽን የሶፍት ዌርና ዳታ ማዕከል ቡድን መሪ ወይዘሮ ሰላም ተስፋዬ አማካይነት በሲስተሙ ስለተካተቱ ስድስት ሞጁሎች ገለጻ ተደርጉዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ ልማትና ማስፋፋት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ደረጀ ዳኜ ስልጠናው በዋናነት በሲስተሙ ከተካተቱ ሞጅሎች መካከል ከስርአተ ትምህርቱ አተገባበር ጋር በቀጥታ የሚገናኙትን ሶስት ሞጁሎች ማለትም ለርኒንግ ማኔጅመንት ሲስተም ፤ ዲጂታል ላይብረሪ ሲስተም እንዲሁም ላይብረሪይ ማኔጅመንት ሲስተም ዙሪያ ግንዛቤ ለመፍጠር ታስቦ መዘጋጀቱን አስታውቀዋል።

ዳይሬክተሩ አያይዘውም የስርአተ ትምህርት ባለሙያዎቹ በስልጠናው ያገኙትን በግንዛቤ መሰረት በማድረግ በየትምህርት አይነቶቹና በየክፍል ደረጃው የመማሪያና አጋዥ መጽሀፍቶችን ጨምሮ ሌሎች ለመማር ማስተማር ስራው የሚያግዙ ዲጂታል ይዘቶችን ሲስተሙ ላይ በመጫን ተማሪዎችን ተጠቃሚ ማድረግ እንደሚገባቸው ጠቁመው በቀጣይ በየደረጃው ለሚገኙ የስርአተ ትምህርት ባለሙያዎች ተመሳሳይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና የሚሰጥ መሆኑን አመላክተዋል፡፡

0 Comments