የአንደኛ ሩብ አመት ሪፎርም ስራዎች አፈጻጸም ድጋፍና ክትትል ተደረገ።

by | ዜና

(ጥቅምት 12/2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የሪፎርምና አገልግሎት አሰጣጥ ክትትልና ድጋፍ ምዘና ዳይሬክቶሬት በቢሮው ለሚገኙ ዳይሬክቶሬቶች በሪፎርምና አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ድጋፍና ክትትል ማድረጉን አሳውቋል፡፡

ድጋፍና ክትትሉ በመደበኛ እንዲሁም በሪፎርም ስራዎች ስኬታማ የስራ አፈጻጸም መኖሩን የስራ ክፍሉ የሚያረጋግጥበት አንዱ መንገድ መሆኑን የገለጹት የሪፎርምና አገልግሎት አሰጣጥ ክትትል ድጋፍና ምዘና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ተስፋገኘሁ ለገሰ በየስራ ክፍሉ ያሉ ስራዎች ወጥ የሆነ አፈጻጸም እንዲኖራቸው ብሎም ተገቢ የአገልግሎት አሰጣጥ መኖሩን በማየት ክፍተት ያለበትን የስራ ክፍል ለመደገፍ እንደሚያስችል አብራርተዋል፡፡ ድጋፍና ክትትል ተግባሩ በዚህ በጀት አመት ለሁለተኛ ጊዜ የተከናወነ መሆኑን ያነሱት ዳይሬክተሩ በቀጣይ ለሚደረግ የምዘና ስራ የማንቃትና የዝግጅት ምእራፍ አፈጻጸምን ለማየት እንደሚያስችል አብራርተዋል፡፡

የሪፎርምና አገልግሎት አሰጣጥ ክትትል ድጋፍና ምዘና ቡድን መሪ አቶ ሀፍቱ ብርሀኑ በበኩላቸው ቢሮው የአገልግሎት አሰጣጡን ለማሻሻል ትኩረት በማድረግ እየሰራ መሆኑን አስታውሰው፤ የሪፎርምና አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ድጋፍና ክትትል ለማድረግ በክፍለ ከተማ 8 የትኩረት መስኮችና 45 ዝርዝር ተግባራት በማእከል ደረጃም 7 የትኩረት መስኮችና 40 ዝርዝር ተግባራት ያካተተ ቼክሊስት በማዘጋጀት ስራው እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በድጋፍና ክትትሉ በቢሮና በክፍለ ከተማ ከ40 በላይ የሚሆኑ ባለሙያዎች መሳተፋቸውንና በቼክሊስቱ መሰረት የድጋፍና ክትትል ተግባሩን በማከናወን ቀጣይ በግኝቶች ላይ የጋራ ውይይት እንደሚደረግ ከስራክፍሉ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

0 Comments