(ጥቅምት 2/2017 ዓ.ም) ኦረንቴሽኑ በድጋፍና ክትትል መርሀግብሩ ለሚሳተፉ የክፍለ ከተማና ወረዳ ሱፐርቫይዘሮች እንዲሁም ለስርአተ ትምህርት ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች የተሰጠ ሲሆን የቢሮው የስርአተ ትምህርት ማበልጸጊያና ትግበራ ዳይራክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ታለማ እና የአፋን ኦሮሞ ስርአተ ትምህርት ማበልጸጊያና ትግበራ ዳይራክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ተሸመ ቀናሳ የቼክሊስቱን ይዘት በዝርዝር የማስተዋወቅ ተግባር አከናውነዋል።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የቢሮ ኃላፊ አማካሪ ወይዘሮ አበበች ነጋሽ በመርሀ ግብሩ መክፈቻ ባስተላለፉት መልዕክት ተማሪዎች በሒሳብና እንግሊዘኛ የትምህርት አይነቶች ውጤታማ መሆን ከቻሉ በሌሎች የትምህርት አይነቶች የተሻለ ውጤት የማስመዝገባቸው ሁኔታ ከፍተኛ በመሆኑ ቢሮው ከ1ኛ እስከ 12ኛ ክፍል የሚማሩ ተማሪዎች በሁለቱ የትምህርት አይነቶች ውጤታማ እንዲሆኑ ስትራቴጂ ነድፎና ጥናት አስጠንቶ ተግባራዊ እንቅስቃሴ መጀመሩን ጠቁመው ስትራቴጂው ተግባራዊ ስለመሆኑ ድጋፍና ክትትል በማድረግ ተግባር የሚሳተፉ ሱፐርቫይዘሮችም ሆኑ የትምህርት ባለሙያዎች ቼክሊስቱን በአግባቡ በመሙላት ለሚመለከተው አካል ሪፖርት ማድረግ እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል።
የቢሮው የአጠቃላይ ትምህርት ሱፐርቪዥን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አብዱልበር መሀመድ በበኩላቸው ቀደም ሲል ተመሳሳይ መርሀ ግብር ከተለያዩ አካላት ጋር ለሁለት ጊዜ መካሄዱን ጠቁመው በትምህርት ቤቶቹ የሚካሄደው የድጋፍና ክትትል መርሀ ግብር ከመጪው ሰኞ ጀምሮ ለተከታታይ ሶስት ቀናት እንደሚካሄድ በመግለጽ በቀጣይ በድጋፍና ክትትል ሂደቱ የሚቀርቡ ግኝቶችን መሰረት በማድረግ የተለያዩ ተግባራት የሚከናወኑ መሆኑንም አመላክተዋል።
በሒሳብና እንግሊዘኛ ትምህርት ስትራቴጂ መሰረት በትምህርት ተቋማት ለሚደረግ የድጋፍና ክትትል በተዘጋጀ ቼክ ሊስት ዙሪያ ኦረንቴሽን ተሰጠ።
0 Comments