(መስከረም 30/2017 ዓ.ም) ስልጠናው በኢፌድሪ ትምህርት ሚኒስቴር የበለጸገውን kobo tool box ሶፍትዌር በመጠቀም መረጃዎች እንዴት እንደሚሞሉ እና ፈጣን መረጃ (quick data)ለመሰብሰብ በተዘጋጀ ቅጽ ዙሪያ መሰጠቱን ከስራ ክፍሉ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ትምህርት መረጃ ዝግጅትና አስተዳደር ቡድን መሪ አቶ ደስታ አብረሀም በስልጠናው መክፈቻ ባስተላለፉት መልዕክት የኢፌድሪ ትምህርት ሚኒስቴር አጠቃላይ የትምህርት መረጃዎችን በአግባቡ ለማደራጀት kobo tool box የተሰኘ ሶፍት ዌር አበልጽጎ ለክልሎች መላኩን ጠቁመው ሶፍትዌሩ የተማሪዎችን እና የትምህርት ተቋማትን ብዛት ጨምሮ አጠቃላይ የትምህርት መረጃዎች የሚሞሉበት እንደመሆኑ የስልጠናው ተሳታፊዎች ሶፍትዌሩን ተጠቅመው መረጃዎችን በየወረዳው በአግባቡ መሙላት እንዲችሉ ታስቦ ስልጠናው መዘጋጀቱን አመላክተዋል።
በመርሀ ግብሩ የቢሮው የአጠቃላይ የትምህርት ስርአት መረጃ ዝግጅትና አስተዳደር ባለሙያ አቶ ጋሻው አክሊሉ በየትምህርት ቤቱ ኦን ላይን የተካሄደውን የ2017 ዓ.ም የተማሪ ምዝገባን ጨምሮ የተለያዩ መረጃዎችን ለመሰብሰብ በተዘጋጀ የፈጣን መረጃ መሰብሰቢያ ቅጽ ዙሪያ ገለጻ ያደረጉ ሲሆን የስልጠናው ተሳታፊዎችም በቅጹ መሰረት መረጃዎችን በፍጥነት በመሙላት ለሚመለከተው አካል ተደራሽ ማድረግ እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል።
የአጠቃላይ ትምህርት መረጃ ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ለክፍለ ከተማና ወረዳ የዘርፉ ባለሙያዎች ስልጠና ሰጠ።
0 Comments