የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ማኔጅመንት አባላት የ2017 የትምህርት ዘመንን የአንደኛ ሩብ ዓመት እቅድ አፈጻጸም ገመገሙ።

by | ዜና


(መስከረም 29/2017 ዓ.ም) በግምገማው የ2017 የትምህርት ዘመን የአንደኛ ሩብ ዓመት መሪ እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በቢሮ እቅድ በጀት ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በአቶ ጌታሁን ለማ እና የመልካም አስተዳደር ፤ የብልሹ አስራርና የአገልግሎት አሰጣጥ እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በቢሮው የለውጥና መልካም አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በሆኑት በአቶ ተስፋአገኘሁ ለገሰ ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል።

በቀረቡት ሪፖርቶች ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በ2017 የትምህርት ዘመን በቅድመ ዝግጅት ተግባራት በርካታ አመርቂ ስራዎች ማከናወኑ የተገለጸ ሲሆን በግምገማዉ ላይ ሪፖርቱ በቀጣይ ከአጠቃላይ ካውንስል አባላት ፣ ከቢሮ ሰራተኞችና ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተደርጎበት የሚዳብር መሆኑ ተመላክቷል፡፡

በግምገማው ላይ የበ2017 የትምህርት ዘመን በ3 ወራት ውስጥ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የትምህርት ልማት ስራው ውጤታማ እንዲሆን በርካታ ተግባራትን ማከናወኑ የተገለጸ ሲሆን በቀጣይ የትምህርት ዘመኑ እቅድ ከዚህ ቀደም ከነበረው አፈጻጸም በበለጠ ደረጃ ውጤታማ እንዲሆን በትጋት መስራት ከሁሉም የትምህርት ባለድርሻ አካላት እንደሚጠበቅ ተጠቁሟል።

0 Comments