(መስከረም 22/2017 ዓ.ም) ድጋፍና ክትትሉ በ2016 ዓ.ም የቀዳማይ ልጅነት ፕሮግራምን ተግባራዊ አድርገው ትራንስፎርም እንዲሆኑ በተለዩ 40 የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እንዲሁም በተመሳሳይ ለ2017 ዓ.ም በተለዩ 60 ተቋማት የተካሄደ ሲሆን ግብረ መልሱ በቢሮው የቀዳማይ ልጅነት ጉዳዮች ቡድን መሪ ወይዘሮ ፍሬሕይወት በቀለ ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ወንድሙ ኡመር በመርሀ ግብሩ መክፈቻ ባስተላለፉት መልዕክት የቀዳማይ ልጅነት ፕሮግራም ከተማ አስተዳደሩ ቅድሚያ ሰጥቶ ተግባራዊ ከሚያደርጋቸው ፕሮግራሞች መካከል አንዱ መሆኑን ጠቁመው በትምህርት ሴክተሩ ፕሮግራሙ በቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በመተግበር ላይ መሆኑን አስታውቀዋል።
ምክትል ቢሮ ኃላፊው አያይዘውም በቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ፕሮግራሙ በአግባቡ ተግባራዊ እንዲሆን በየደረጃው የሚገኙ ሱፐርቫይዘሮች ለተቋማቱ የተሰራጩ ግብአቶች ለሚፈለገው አገልግሎት መዋላቸውንም ሆነ ጫወታን መሰረት ያደረገ የማስተማር ስነዘዴ በአግባቡ ተግባራዊ መደረጉን በድጋፍና ክትትል ማረጋገጥ እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል።
የቢሮው የዘርፈ ብዙና ቀዳማይ ልጅነት ትግበራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወይዘሮ በላይነሽ የሻው በበኩላቸው በ2016 ዓ.ም የቀዳማይ ልጅነት ፕሮግራምን ተግባራዊ አድርገው ትራንስፎርም እንዲሆኑ በተለዩ 40 የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እና በተመሳሳይ ለ2017 ዓ.ም በተለዩ 60 ተቋማት በተካሄደ የድጋፍና ክትትል ግብረመልስ ዙሪያ በየደረጃው ከሚገኙ ሱፐርቫይዘሮች ጋር በመወያየት በቀጣይ ውጤታማ ስራ ለመስራት ታስቦ መርሀ ግብሩ መዘጋጀቱን አስታውቀዋል።
በቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በተካሄደ የድጋፍና ክትትል ግብረ መልስ ዙሪያ በየደረጃው ከሚገኙ ሱፐርቫይዘሮች ጋር ውይይት ተካሄደ።
0 Comments