ከኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ ጋር ለመምህራን የጋራ መኖሪያ ቤት ለመገንባት የሚያስችል የመጀመሪያ ዙር የብድር ውል ስምምነት ሰነድ ላይ ውይይት ተደረገ::

by | ዜና


(መስከረም 21/2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የመኖሪያ ቤት የሌላቸው መምህራን ተደራጅተው የቤት ባለቤት እንዲሆኑ በርካታ ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል፡፡ በዛሬው እለትም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፣ የአዲስ አበባ መምህራን ማህበር እና የአዲስ አበባ ህብረት ሥራ ኮሚሽን ከኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ ጋር ለመምህራን የጋራ ቤት ለመገንባት በሚያስችል የብድር ውል ስምምነት ሰነድ ላይ የመጀመሪያ ዙር የጋራ ውይይት አድርገዋል::

በውይይቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ፣ የአዲስ አበባ መምህራን ማህበር ፕሬዝዳንት አቶ ድንቃለም ቶሎሳ ፣ የአዲስ አበባ ህብረት ሥራ ኮሚሽን ኮሚሽነር ልእልቲ ግደይ ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ አሊ ከማል እና የኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ ኃላፊዎች በተገኙበት የተካሄደ ሲሆን በዋናነት የብድር ውል ስምምነት ፣ የብድር ክፍያ ቆይታ ጊዜና የወለድ ክፍያን አስመልክቶ ውይይት ተደርጓል::

0 Comments