ለአካቶ ትምህርት ውጤታማነት በትኩረት እንደሚሰራ ተገለጸ፡፡

by | ዜና


(መስከረም 20/2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የሰኞ ማለዳ ከስራ ሰዓት መግቢያ በፊት የሚያዘጋጀው የሰራተኞች የዕውቀት ሽግግር መርሀ ግብር በዛሬው ዕለት የተካሄደ ሲሆን በመድረኩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ፣ የቢሮ ማኔጅመንት አባላትና ሰራተኞች ተሳታፊ ሆነዋል።

በመርሀ ግብሩ በአካቶ ትምህርት ጽንሰ ሀሳብ ላይ መሰረት ያደረግ ሰነድ በአቶ ዳንኤል አስራት በቢሮ የልዩ ፍላጎት ጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ ትምህርት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የቀረበ ሲሆን በመድረኩ ማጠቃለያ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ለዘርፉ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት በቢሮ ደረጃ ዳሬክቶሬት ተቋቁሞና የአካቶ ትምህርት በከተማ አስተዳደሩ እየተተገበረ መሆኑን በመጥቀስ በቀጣይም ከዚህ ቀደም ሲሰራበት ከነበረው በላቀ ደረጃ ለስራዉ ውጤታማነት በትጋት የሚሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

0 Comments