(የካቲት 17/2017 ዓ.ም) በዛሬው መርሀ ግብር የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ልማትና ማስፋፋት ዳይሬክቶሬት፣የትምህርት መረጃ ዝግጅትና አስተዳደር እንዲሁም የትምህርት ግብአት አቅርቦትና ስርጭት ዳይሬክቶሬት የጥር ወር እቅድ አፈጻጸም እና በየካቲት ወር ውስጥ የታቀዱና እስካሁን የተከናወኑ ተግባራት ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊና የዘርፉ ኃላፊ አቶ ሳምሶን መለሰ ቢሮው የተማሪዎችን ውጤትና ስነምግባር ለማሻሻል እያከናወነ የሚገኘው ስራ ውጤታማ እንዲሆን በሶስቱ ዳይሬክቶሬቶች የሚከናወኑ ተግባራት የሚያበረክቱት አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን ጠቁመው ስራ ክፍሎቹ በጥር ወር እና በየካቲት ወር ውስጥ ታቅደዉ እስካሁን የተከናወኑ ተግባራትን ከእቅዳቸው በመነሳት ያከናወኗቸውን ተግባራት በመገምገም በቀጣይ የተሻለ ስራ ለመስራት ታስቦ ውይይቱ እንደመካሄዱ ስራ ክፍሎቹም በጥንካሬ ያሉ አፈጻጸማቸውን በማስቀጠልም ሆነ በሂደት የተስተዋሉ ክፍተቶችን በማሻሻል በቀጣይ የተሻለ ስራ መስራት እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል።
በመርሀ ግብሩ የቢሮው የሶፍትዌር ሲስተምና አስተዳደር ቡድን መሪ ወይዘሮ ሰላም ተስፋዬ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ልማትና ማስፋፋት ዳይሬክቶሬት የጥር ወር እቅድ አፈጻጸም እንዲሁም የትምህርት መረጃ ዝግጅትና አስተዳደር ቡድን መሪ አቶ ደስታ አብረሀም እና የትምህርት ግብአት አቅርቦትና ስርጭት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ምስራቅ ብርሀነ መስቀል የየስራ ክፍላቸውን የጥር ወር እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት አቅርበው ውይይት በማድረግና በቀጣይ በሚከናወኑ ተግባራትን አስመልክቶ አቅጣጫ በማስቀመጥ ውይይቱ ተጠናቋል።
0 Comments