(የካቲት 17/2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የሰኞ ማለዳ ከስራ ሰዓት መግቢያ በፊት የሚያዘጋጀው የሰራተኞች የዕውቀት ሽግግር መርሀ ግብር የተካሄደ ሲሆን በመድረኩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ፣ ማኔጅመንት አባላትና ሰራተኞች ተሳታፊ ሆነዋል።
በመርሀ ግብሩ ላይ በኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ የቋንቋ የስነጽሁፍና የሀገር በቀል እውቅት መምህር በሆኑት በዶ/ር ገመቹ ዳዲ የአመራርነት ጥበብ በትምህርት ሴክተር በሚል ርዕሰ ጉዳይ ላይ እውቀታቸዉን ያካፈሉ ሲሆን በመድረኩ ማጠቃለያ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ የአመራርነት ጥበብ ለስራ ለውጤታማነት ከፍተኛ ድርሻ እንዳለዉ በመጥቀስ የቀረበዉ ሰነድ የትምህርት አመራሮችና ባለሙያዎች በሰራ ሂደት ውስጥ የሚያከናውናቸዉን ጉዳዮች ሊያዩበት የሚገባውን የእይታ አድማስ ያሰፋና እውቀትን ያስጨበጥ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
0 Comments