የልዩ ፍላጎትና የጎለማሶች ትምህርት ዳይሬክቶሬት በ2016 ዓ.ም ባከናወናቸውና በ2017 ዓ.ም በዘርፉ ባቀዳቸው ተግባራት ዙሪያ ውይይት ተካሄደ፡፡

by | ዜና

(መስከረም 06/2017 ዓ.ም) በውይይቱ የክፍለከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት የዘርፉ ቡድን መሪዎች የተሳተፉ ሲሆን ፍላጎትና የጎለማየልዩ ሶች ትምህርት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዳንኤል አስራት በ2016 ዓ.ም የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራትን እና በ2017ዓ.ም የታቀዱ ተግባራት አቅርበው ውይይት ተካሂዱዋል፡፡

በውይይቱ በ2016 ዓ.ም በአፈጸጸም የተለዩ ክፍተቶችን በመለየት በ2017 ዓ.ም የተሻለ ስራ ለመስራት የሚያስችሉ ሀሳቦች መነሳታቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የልዩ ፍላጎትና የጎልማሶች ትምህርት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዳንኤል አስራት አስታውቀዋል፡፡

ዳይሬክተሩ አያይዘውም በ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ሁሉም ትምህርትቤቶች የልዩ ፍላጎት ተማሪዎችን በአግባቡ ተቀብለው በትምህርታቸው ውጤታማ እንዲሆኑ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ መወጣት እንደሚገባቸው ጠቁመው ከጎልማሶች ትምህርት ጋር በተገናኘም ክረምት የተጀመረውን ትምህርት በፍጥነት በማጠናቀቅ የጎልማሶቹን የመጻፍና የማስላት ክህሎት በማዳበር የአውቅና ሰርተፊኬት እንደሚሰጥ አመላክተዋል፡፡

0 Comments