(ጥር 28/2017 ዓ.ም) በመስክ ምልከታው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱን ጨምሮ የቢሮ አማካሪ አቶ ጥላሁን ፍቃዱ ፣ ምክትል ቢሮ ኃላፊዎቹ አቶ ወንድሙ ኡመር እና አቶ ሳምሶን መለሰ እንዲሁም የአዲስ አበባ ከተማ መምህራን ማህበር ፕሬዘዳንት አቶ ድንቃለም ቶሎሳና የየካ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፈይሳ ወዳጆ ተሳታፊ ሆነዋል።
ከተማ አስተዳደሩ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ የትምህርት ተቋማትን በመገንባት የተማሪ ክፍል ጥምርታውን ወደ ስታንዳርድ በማምጣት ላይ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ጠቁመው ዛሬ ምልከታ በተደረገባቸው ትምህርት ቤቶች ያለው የተማሪ ቁጥር ከፍተኛ በመሆኑ በተቋማቱ የማስፋፊያ ግንባታ በማከናወን ወደ ስታንዳርዱ የማምጣት ስራ እንደሚሰራ ጠቅሰዋል።
የመስክ ምልከታው በክፍለ ከተማው በሚገኙት ዳንሴ ፣ አንቆርጫ እና ካራሎ ትምህርት ቤቶች የተካሄደ ሲሆን አመራሮቹ በትምህርት ተቋማቱ በመገኘት የመማሪያ ክፍሎችን ጨምሮ የመጸዳጃና አጠቃላይ የምድረ ግቢ ይዞታቸውን ተመልክተዋል።
0 Comments