ለሥራ ክፍሎችና አዳሪ ትምህርት ቤቶች በ2017 የትምህርት ዘመን በተደረገ የ6 ወራት ክትትልና ድጋፍ ማጠቃለያ ሪፖርት ላይ ውይይት ተካሄደ::

by | ዜና

(ጥር 23/2017 ዓ.ም) የሪፎርም አገልግሎት አሰጣጥ ክትትል ድጋፍና ምዘና ዳይሬክቶሬት በ2017 በጀት አመት 6 ወራት የሥራ ክፍሎችና አዳሪ ትምህርት ቤቶች ያካሄደው ክትትልና ድጋፍ ማጠቃለያ ሪፖርት የሚመለከታቸው አካላት በተገኙበት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል:: በሪፖርቱ በክትትልና ድጋፍ ተግባር በእጥረትና ጥንካሬ የታዩ ግኝቶች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል ::

የድጋፍና ክትትሉ ሪፖርት ሲቀርብ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አማካሪ ወ/ሮ አበበች ነጋሽ ፣ የቢሮ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሲሳይ እንዳለ ፣ የቢሮ አማካሪ አቶ ጥላሁን ፈቃዱ ፣ የቢሮው ዳይሬክተሮች እና ቡድን መሪዎች እንዲሁም የሁለቱ አዳሪ ትምህርት ቤቶች ርዕሰ መምህራን ተገኝተዋል::

የቢሮ ኃላፊ አማካሪና የሪፎርም አገልግሎት ክትትልና ድጋፍ ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ አበበች ነጋሽ ሪፓርቱ ለሚመለከታቸው አካላት መቅረቡ የሪፎርም አገልግሎት አሰጣጥ ድጋፍ ክትትል ሥራዎች ላይ ዳይሬክቶሬቶቹና አዳሪ ትምህርት ቤቶቹ ያከናወኗቸው ዋና ዋና ተግባራት አፈፃፀም በጥንካሬና በእጥረት የታዩ ነጥቦች በማየት ቀጣይ አሰራርን ለማስተካከልና ተቀራራቢ አፈፃፀም ለማስመዝገብ ብሎም በግብረ መልሱ መሰረት ማስተካከያ በማድረግ የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት እንደሚረዳ ገልፀዋል ::

የቢሮ አማካሪ አቶ ጥላሁን ፍቃዱ በበኩላቸው ግብረ መልሱ በቀጣይ ለሚከናወኑ ተግባራት ውጤታማነት እንደ ማንቂያ በመውሰድ ለተሻለ ሥራ ራስን ለማነሳሳትና የፍክክር መንፈስ ለመፍጠር ያግዛል ብለዋል:: አያይዘውም በየጊዜው የሚደረገው ድጋፍና ክትትል ተቀራራቢ ውጤት ከማስገኘትና አቅም ከማሳደግ አንፃር የራሱን በጎ ተፅእኖ እያሳደረ መምጣቱን ተናግረዋል ::

የቢሮ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሲሳይ እንዳለ በድጋፍና ክትትሉ የተሰጡ ውጤቶች ለቀጣይ ሥራዎችን በተሻለ ትጋት ለመስራት የሚያግዙ መሆናቸውን በመውሰድ ጥቅም ላይ ማዋል እንዲቻል አሳስበዋል::

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የሪፎርም አገልግሎት አሰጣጥ ክትትል ድጋፍና ምዘና ዳይሬክተር ተወካይ አቶ ፋንታሁን እያዩ የሪፎርም ሥራዎችን ውጤታማ ለማድረግ ተከታታይ ድጋፍና ክትትል መደረጉ ጠቀሰው በክትትልና ድጋፍ የሚሰጡ ግብረመልሶች ዳይሬክቶሬቶቹ ቀጣይ ስራን ለማሻሻል የሚጠቀሙበት መሆን አለበት በማለት አሳስበዋል::

0 Comments