(ጥር 16/2017 ዓ.ም) የአሰልጣኞች ስልጠናው ከየትምህርትቤቱ ለተውጣጡ የአይሲቲ መምህራን ለተከታታይ 6 ቀናት በሁሉም ክፍለከተሞች በተቋቋሙ 11 የስልጠና ጣቢያዎች እየተሰጠ እንደሚገኝ ከኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ልማትና ማስፋፋት ዳይሬክቶሬት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ልማትና ማስፋፋት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ደረጀ ዳኜ የአሰልጣኞች ስልጠናው ቀደም ሲል ተመሳሳይ ስልጠና በወሰዱ አካላት እየተሰጠ እንደሚገኝ ጠቁመው አሁን እየተሰጠ የሚገኘው ስልጠና የኢ-ስኩል ሲስተሙን በአግባቡ ተግባራዊ በማድረግ ለተማሪዎች በቴክኖሎጂ የተደገፈ የመማር ማስተማር አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ እንደሚያስችል አስረድተዋል፡፡
የቢሮው የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የሲሰተም አስተዳደር ቡድን መሪ ወ/ሮ ሰላም ተስፋዩ በበኩላቸው የአሰልጣኞች ስልጠናውን በመውሰድ ላይ የሚገኙት የአይ ሲቲ መምህራን በቀጣይ በየትምህርትቤቶቻቸው በሁሉም የትምህርት አይነቶች ለሚያስተምሩ መምህራን በተመሳሳይ ከሲስተሙ ጋር በተገናኘ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እንደሚሰጡ ገልጸዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ከኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ልማትና ማስፋፋት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ደረጀ ዳኜ እና የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የመሰረተ ልማትና ዝርጋታ ቡድን መሪ አቶ ሚካኤል መስፍን በዛሬው እለት የስልጠናውን ሂደት በተመለከተ በተወሰኑ የስልጠና ጣቢያዎች በመገኘት ምልከታ አካሂደዋል፡፡
0 Comments