(ጥር 9/2017 ዓ.ም) ብቃት የማረጋገጡን ስራ ከመንግስትና ከግል ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ መምህራን እና የክፍለ ከተማ የዘርፉ ቡድን መሪዎች መስራታቸውን ከመርሀ ግብሩ አዘጋጆች ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የስርአተ ትምህርት ማበልጸጊያና ትግበራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ታለማ በትምህርት ቤቶች ወጥ የሆነ የተከታታይ ምዘና ስርአት በማስፈን የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥና የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል እንዲቻል ሰነዱ መዘጋጀቱን ገልጸዋል።
ዳይሬክተሩ አያይዘውም በብቃት ማረጋገጥ ሂደቱ በመምህራኑ የሚሰጡ የማስተካከያ እና የማሻሻያ ሀሳቦችን በማካተት በቀጣይ ሰነዱን ወደ ተግባር የማስገባት ስራ የሚሰራ መሆኑን ጠቁመው ስራ ክፍሉ ተገቢውን ድጋፍና ክትትል የማድረግ ተግባሩን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አመላክተዋል።
0 Comments