ለቢሮው አጠቃላይ ሰራተኞች የህይወት ክህሎት ስልጠና ተሰጠ።

by | ዜና

(ጥር 9/2017 ዓ.ም) ስልጠናው በዘርፈ ብዙ ጉዳዮች ቡድን አስተባባሪነት የተዘጋጀ ሲሆን የህይወት ክህሎት ስልጠናው በዘርፉ የረጅም ጊዜ የማሰልጠን ልምድ ባላቸው እና ከጤና ቢሮ በመጡት በአቶ ስንታየሁ ጎሹ አማካይነት ነው የተሰጠው።

                   

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የዘርፈ ብዙ ጉዳዮች ትግበራ ቡድን መሪ አቶ ይልማ ተሾመ በስልጠናው መክፈቻ ባስተላለፉት መልዕክት ሰራተኛው በህይወት ክህሎት ጽንሰ ሀሳብ ዙሪያ በቂ ግንዛቤ በመፍጠር በእለት ከእለት ህይወቱ የሚያጋጥሙትን ችግሮች ቀርፎ በስራ ገበታው ውጤታማ እንዲሆን በማሰብ ስልጠናው መዘጋጀቱን ገልጸው ስራ ክፍሉ በቢሮ ደረጃ ከሚሰጠው የህይወት ክህሎት ስልጠና ባሻገር እስከ ትምህርት ቤት ድረስ ድረስ ተመሳሳይ ስልጠና በመስጠት ላይ እንደሚገኝ አስገንዝበዋል።

የህይወት ክህሎት ማለት ሰዎች በህይወት ዘመናቸው የሚያዳብሩት ጥበብ እንደመሆኑ የቢሮው ሰራተኞች በጉዳዩ ላይ በቂ ግንዛቤ ፈጥረው በህይወታቸው ውጤታማ እንዲሆኑ በዘርፉ የካበተ ልምድ ባላቸው ባላቸው ባለሙያ ስልጠናው መሰጠቱን የቢሮው የኤች አይቪ ኤድስ መከላከል ባለሙያ ገንዘብ ደሳለኝ ጠቁመው ሰራተኞቹም በስልጠናው ያገኙትን ግንዛቤ መሰረት በማድረግ የኑሮ ዘይቤያቸውን ውጤታማ ማድረግ እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል።

0 Comments