የአጠቃላይ ትምህርት ጥናትና ምርምር ዳይሬክቶሬት ለምክትል ርዕ ሳነ መምህራን ሁለተኛ ዙር ስልጠና ሰጠ።

by | ዜና

(ጥር 3/2017 ዓ.ም) ስልጠናው በትምህርት ቤት ደረጃ በተለይም በመምህራን የሚካሄድ የጥናትና ምርምር ስራ አስፈላጊነትን መሰረት አድርጎ የተሰጠ ሲሆን በመርሀግብሩ ከብርሀን የአይነስውራን አዳሪ ፣ከእቴጌ መነን የልጃገረዶች እንዲሁም ከገላን የወንዶች አዳሪ ትምህርት ቤት እና ከተለያዩ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ የመምህራን ልማት ምክትል ርዕሳነ መምህራን ተሳታፊ ሆነዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ትምህርት ጥናትና ምርምር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዮሀንስ ተስፋዬ በስልጠናው መክፈቻ ባስተላለፉት መልዕክት በትምህርት ቤት ደረጃ በተለይም በመምህራን የሚሰሩ የጥናትና ምርምር ስራዎች በመማር ማስተማር ሂደቱ የሚስተዋሉ ችግሮች እንዲቀረፉ የሚኖራቸው አስተዋጽኦ ከፍተኛ በመሆኑ በየተቋማቱ የሚገኙ የመምህራን ልማት ምክትል ርዕሳነ መምህራን ተገቢውን ድጋፍና ክትትል ማድረግ እንዲችሉ በማሰብ ስልጠናው መዘጋጀቱን አመላክተዋል።

ዳይሬክተሩ አያይዘውም በቀጣይ ስራ ክፍሉ በየክፍለ ከተማው ከተቋቋሙ የጥናትና ምርምር ኮሚቴዎች ጋር በጋራ በመሆን በሚያደርገው ድጋፍና ክትትል በትምህርት ቤት ደረጃ የሚሰሩ የጥናትና ምርምር ስራዎችን በመገምገም ዕውቅና እንዲያገኙ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እንደሚሰራ አስታውቀዋል።

የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናው በቢሮው የአጠቃላይ ትምህርት ጥናትና ምርምር ቡድን መሪ አቶ መለሰ ዘለቀ አማካይነት የተሰጠ ሲሆን የስልጠናው ተሳታፊዎችም በተሰጠው ስልጠና ዙሪያ ውይይት አካሂደዋል።

በስልጠናው ከሶስቱ አዳሪ ትምህርት ቤቶች በተጨማሪ ከየካ፣ቦሌ፣ለሚ ኩራ፣አቃቂ ቃሊቲ፣ቂርቆስ እና ንፋስል ላፍቶ ክፍለ ከተሞች ከሚገኙ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ የመምህራን ልማት ምክትል ርዕሳነ መምህራን የተሳተፉ ሲሆን ቀደም ሲል በቀሩ ክፍለ ከተሞች ለሚገኙ ምክትል ርዕሳነ መምህራን ተመሳሳይ ስልጠና መሰጠቱ ይታወቃል።

0 Comments