(ታህሳስ 24/2017 ዓ.ም) ድጋፍና ክትትሉ በነገው እለት በክፍለከተማ ትምህርት ጽህፈትቤቶች የሚካሄድ ሲሆን በሪፎርም አገልግሎት አሰጣጥ ክትትል ድጋፍና ምዘና ዳይሬክቶሬት አማካይነት በድጋፍና ክትትሉ ለሚሳተፉ የቢሮው ባለሙያዎች በተዘጋጀው መስፈርት ዙሪያ ኦረንቴሽን ተሰቱዋል፡፡
ቀደም ሲል ከቢሮው ጀምሮ እስከ ትምህርት ቤት ድረስ የዝግጅት ምዕራፍ አፈጻጸምን እና የተግባር ምዕራፍ አጀማመርን መሰረት ያደረገ ድጋፍና ክትትል መካሄዱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የሪፎርም አገልግሎት አሰጣጥ ክትትል ድጋፍና ምዘና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሀፍቱ ብርሀኑ ገልጸው አሁን የሚደረገው ድጋፍና ክትትል ቀደም ሲል በተካሄደ ተመሳሳይ ተግባር ትምህርት ጽህፈት ቤቶቹ የተሰጡ ግብረመልሶችን የጋራ አድርገው ምንያህል የማስተካከያ ስራ እንደሰሩ ለማየት እንደሚያስችል አስረድተዋል፡፡
ዳይሬክተሩ አያይዘውም አሁን የሚደረገው የድጋፍና ክትትል ስራ ሲጠናቀቅ በቀጣይ ከቢሮ ጀምሮ እስከ ትምህርት ቤት ድረስ የአንደኛ መንፈቅ አመት አፈጻጸምን መሰረት ያደረገ ምዘና የሚካሄድ መሆኑን ጠቁመው ስራ ክፍሉም ምዘናውን ለማካሄድ የሚያስችል ቅድመ ዝግጅት ማድረጉን አስገንዝበዋል፡፡
0 Comments