(ታህሳስ 18/2017 ዓ.ም) ምክትል ቢሮ ኃላፊው በሚያስተባብሩት ዘርፍ የሚገኙ ስራ ክፍሎችን ማለትም የቢሮው የትምህርት ቤት መሻሻል ዳይሬክቶሬት ፣ የዘርፈ ብዙና ቀዳማይ ልጅነት ትግበራ ዳይሬክቶሬት እንዲሁም የልዩ ፍላጎትና ጎልማሶች ትምህርት ዳይሬክቶሬት የ6 ወር እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ገምግመዋል።
በውይይቱ በሶስቱ ዳይሬክቶሬቶች ስር የሚገኙ ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች የተሳተፉ ሲሆን የዳይሬክቶሬቶቹ የ2017ዓ.ም 6ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ በተሳታፊዎች ውይይት ተካሂዷል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ እና የዘርፉ አስተባባሪ አቶ ወንድሙ ዑመር በስድስቱ ወራት በሶስቱ ዳይሬክቶሬቶች በርካታ ውጤታማ ተግባራት መከናወናቸውን ገልጸው በዚህ ሂደት የተከናወኑ ጠንካራ አፈጻጸሞችን በማስቀጠልም ሆነ በአፈጻጸም የተስተዋሉ ችግሮችን በመቅረፍ በቀጣይ ውጤታማ ስራ መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
0 Comments