(ታህሳስ 11/2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በትምህርት ልማት ስራዎች ላይ እያካናወናቸው የሚገኙ ተግባራት ያመጡትን ውጤት ለማወቅ እንዲቻል በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የፋይዳ ዳሰሳ ጥናቶችን እያከናወነ የሚገኝ ሲሆን የፋይዳ ጥናቶቹ የደረሱበትን ደረጃ አስመልክቶ ጥናቱን እያከናወኑ ከሚገኙ የቢሮ ዳይሬክተሮች ፣ ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች ጋር ውይይት አካሄዳል፡፡
በውይይቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ ወንድሙ ዑመር ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ አማካሪ ወ/ሮ አበበች ነጋሽ ፣ ጉዳዮ የሚመለከታቸው የቢሮ ዳሬክተሮች ፣ ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች ተሳትፈዋል፡፡
በመድረኩም በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ሳይንሳዊ ይዘትን ጠብቀው እየተከናወኑ የሚገኙ የፋይዳ ዳሰሳ ጥናቶች የሚፈለገዉን ውጤት እንዲያስመዘግቡ በትኩረት መስራት እንደሚገባ አቅጣጫ ተቀምጣል፡፡
0 Comments