የተማሪዎች መረጃ የማጥራት ሥራ ሊጀመር መሆኑ ተገለፀ ::

by | ዜና

(ታህሳስ 9/2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ትምህርት መረጃ ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ከኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ልማትና ማስፋፋት ዳይሬክቶሬት ጋር በጋራ በመሆን በከተማ አስተዳደሩ ስር በሚገኙ 229 ቅድመ አንደኛ ፣ 255 አንደኛና መካከለኛ እና በ85 ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሚገኙ ተማሪዎች መረጃ የማጥራትና የማዛመድ ሥራ ሊያከናውኑ መሆኑ ተገልፃል ::

የአጠቃላይ ትምህርት መረጃ ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክተር አቶ ሃፍቱ ብርሀኑ የመረጃ ማጥራት ስራው ቢሮው እንዲሁም ትምህርት ቤቶች የሚያስተዳድሯቸውን ተማሪዎች መረጃ በአግባቡ እንዲያውቁ ፣ መረጃቸውን ለማደራጀትና መረጃ ለሚጠይቅ ማንኛውም አካል ወቅታዊ ፣ ተአማኒና ጥራት ያለው መረጃ ተደራሽ ለማድረግ እንደሚጠቅም ተናግረዋል::

ዳይሬክተሩ አያይዘውም የመረጃ ማጥራት ስራው በታቀደለት ጊዜ እንዲጠናቀቅ የትምህርት ቤት ርእሳነ መምህራን የተማሪ ስም መጥሪያ አቴንዳንስ ፣ ምዝገባ የተካሄደባቸው ቅፆች እና ፈጣን መረጃ በማቅረብ ባለሙያዎቹ ለሚሰሩት የመረጃ ማጥራት ሥራ መደላድል እንዲፈጥሩ አሳስበዋል፡፡

የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ልማትና ማስፋፋት ዳይሬክተር አቶ ደረጀ ዳኘ በበኩላቸው መረጃ የማጥራት ስራው በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ያለው መረጃ በወረቀት ካለዉ ጋር በማመሳከርና ከሲስተም ጋር በማያያዝ የስራ ክፍሉ ታማኝነት ያለው ፈጣን መረጀ ለማቅረብ እንደሚያስችለው አብራርተዋል::

መረጃ የማጥራትና ማዛመድ ስራው ከታህሳስ 14 እስከ 19/2017 ዓ. ም የሚካሄድ ሲሆን የቢሮውና የክፍለ ከተማ አይሲቲ እና መረጃ ባለሙያዎች እንዲሁም የሁሉም ትምህርት ቤቶች ርእሳነ መምህራን እንደሚሳተፉ ከስራ ክፍሎቹ ያገኘነው መረጃ ያሳያል ::

0 Comments