(የካቲት 14/2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በ2017 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን በከተማ አስተዳደሩ በበይነ መረብ ኦን ላይን ለመስጠት በሚያስችል እቅድ ላይ ከክፍለ ከተማ ICT እና መረጃ ባለሙያዎች ጋር ውይይት አካሂዳል፡፡
በውይይቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ልማት ማስፋፋት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ደረጄ ዳኜ የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ቅድመ ዝግጅትን አስመልክቶ የተዘጋጀን እቅድ አቅርበው ውይይት ተካሄዳል::
አቶ ደረጄ የማስፈጸሚያ እቅዱን ባቀረቡበት ወቅት በለሙያዎች ፈተናዉ በኦላይን የሚሰጥ መሆኑን በመገንዘብ እንዲሁም ከ2016 የትምህርት ዘመን ኦላይን ፈተና አሰጣጥ ላይ ከነበሩ ተግባራት ትምህርት በመውሰድ አስፈላጊ በሆኑ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ላይ መሰረት በማድረግ ከወዲሁ አቅደው መስራት እንደሚጠበቅባቸዉ አሳስበዋል፡፡
0 Comments