የፋይናንስ መመሪያና ደንቦች ላይ ግንዛቤ በመፍጠር የመንግስት ሀብትን በአግባቡ መጠቀም እንደሚገባ ተገለፀ ::

by | ዜና

(ህዳር 6/2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት የፋይናንስ ግልፀኝነት ፣ የፋይናንስ መመሪያዎች እና የስልጠና ምክረ ሀሳብ (Proposal) ዝግጅት ላይ ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል::

ስልጠናው የመንግስት ፋይናንስ አጠቃቀም ላይ ግልፀኝነት በመፍጠር ከብልሹ አሰራር የፀዳ የፋይናንስ አሰራር ለመዘርጋትና ሰራተኞች በሚሰሩት የፋይናንስ ሥራ ውጤታማ አፈፃፀም እንዲኖራቸው ለማስቻል በመመሪያና ደንቦች ላይ ያላቸውን ግንዛቤ ያሰፋል ተብሏል::

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ መክብብ በለጠ ስልጠናውን በሰጡት ወቅት እንዳሉት ሰራተኞች ስራቸውን በቅልጥፍናና በጥራት መስራት እንዲችሉ እንዲሁም በግንዛቤ ክፍተት የሚባክን ውስን ሀብት በአግባቡ የታለመለትን አላማ ማሳካት እንዲችል የክህሎት ማሻሻያ ስልጠና መስጠት አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል ::

አያይዘውም ስልጠናው ሰራተኞች ስለፋይናንስ አሰራር በቂ ግንዛቤ እንዲኖራቸውና ሥራዎችን በተቀራራቢ መልኩ ከመፈፀም ባለፈ በአሰራር ሂደት የሚፈጠሩ አለመግባባቶችን ለመቅረፍ እንደሚረዳ አብራርተዋል::

በስልጠናው የመንግስት ፋይናንስ አስተዳደር መመሪያና ደንብ ፣ ምክረ ሃሳብ (proposal) ሲዘጋጅ መሟላት ያለባቸውን ነጥቦች እንዲሁም የበጀት አደረጃጀትና ስርዓት አላማዎች ላይ የስልጠና ሰነዶች የቀረበ ሲሆን የቢሮው ደጋፊ ሥራ ሂደት ባለሙያዎች ተሳታፊ ሆነዋል::

0 Comments