(መስከረም 29/2017 ዓ.ም) የፈተናና ምዘና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት የ1ኛ ሩብ ዓመት ስራ አፈጻጸም ሪፖርትና የ2017 ዓ.ም የተከለሰ እቅድ ላይ እንዲሁም የፈተና መመሪያ እና የሂሳብና እንግሊዘኛ ትምህርቶችን ውጤት ለማላቅ በፈተና ዘርፍ የሚሰሩ ስራዎች ላይ ትኩረት ያደረጉ ሁለት ሰነዶች ላይ ውይይት አድርጓል፡፡
የፈተናና ምዘና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዲናዖል ጫላ ውይይቱ በስራ ክፍሉ በሩብ አመት የተከናውኑ ስራዎችን ከመገምገም ባለፈ ቀጣይ የተማሪ ውጤትን የላቀ ለማድረግ እየተደረጉ ያሉ ስራዎችና የተማሪ ውጤትን የበለጠ ለማጎልበት በሚያስችል ስታንዳርድ ሰነድ ላይ ውይይት እንደሚደረግ ተናግረዋል፡፡
በውይይቱ ላይ የአጠቃላይ ትምህርት ምዘና አስተዳደር መመሪያ ቁጥር 3/2016 ረቂቅ መመሪያ የቀረበ ሲሆን ሰነዱ ቀደም ሲል ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት የተደረገበት መሆኑና የመተግበሪያ ማንዋሎቹም በአማርኛና አፋን ኦሮሞ ስርዓተ ትምህርቶች ተዘጋጅቶ መቅረቡ ተገልጻል፡፡
መመሪያው በዋናነት የክፍል ውስጥ ተከታታይ ምዘናና ማጠቃለያ ፈተናዎች በምን መልኩ መመራት እንዳለባቸው ፤ በፈተና አሰጣጥ ሂደት ከባለሙያ ከአመራሩና በየደረጃው ካሉ የሚመለከታቸው አካላት የሚጠበቁ ተግባራትና ያለው ተጠያቂነት ምን ድረስ እንደሆነ እንደሚያመለክት ዝርዝር ሃሳብ ቀርቦ በተሳታፊዎቸ ውይይት ተደርጎበታል፡፡
ውይይቱ ለሁለት ቀናት የቢሮው ባለሙያዎች የክፍለከተማ ቡድን መሪዎችና የፈተና ባለሙያዎች በተገኙበት እንደሚካሄድ ከዳይሬክቶሬቱ ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡
0 Comments