የዘርፈ ብዙና ቀዳማይ ልጅነት ትግበራ ዳይሬክቶሬት የዘርፉን የ2017 ዓ.ም የአንደኛ ሩብ አመት እቅድ አፈጻጸም ገመገመ።

by | ዜና

(ጥቅምት 12/2017 ዓ.ም) በመርሀ ግብሩ የክፍለ ከተማ የዘርፈ ብዙ ጉዳዮች ቡድን መሪዎች የተሳተፉ ሲሆን የዳይሬክቶሬቱ እና የተመረጡ ክፍለ ከተሞች ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የዘርፈ ብዙና ቀዳማይ ልጅነት ትግበራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወይዘሮ በላይነሽ የሻው በዘርፉ በ2017 ዓ.ም አንደኛ ሩብ አመት በተከናወኑ ተግባራት ዙሪያ በመወያየት በቀጣይ የተሻለ ስራ ለመስራት ታስቦ ውይይቱ መዘጋጀቱን አስታውቀዋል።

ዳይሬክተሩዋ አያይዘውም በ2017 ዓ.ም አንደኛ ሩብ አመት በዘርፉ ከተከናወኑ ተግባራት መካከል በቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የቀዳማይ ልጅነት ፕሮግራም ተግባራዊ እንዲሆን የተለያዩ የድጋፍና ክትትል ተግባራት መከናወናቸውን በመጥቀስ በየትምህርት ቤቱ የሚገኙ የስርአተ ጾታ እና የፀረ ኤች አይ ቪ ክበባት ተጠናክረው በሚፈለገው ደረጃ ውጤታማ እንዲሆኑ ክትትል መደረጉን አመላክተዋል።

በመርሀግብሩ የቀዳማይ ልጅነት ትግበራ ቡድን መሪ ወይዘሮ ፍሬህይወት በቀለ የዳይሬክቶሬቱን የ2017 ዓ.ም አንደኛ ሩብ አመት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት አቅርበው በተሳታፊዎች ውይይት ተካሂዷል።

0 Comments