(ጥቅምት 11/2017 ዓ.ም) የከንቲባ ፅ/ቤት መልካም አስተዳደርና አቤቱታ ዘርፍ ቡድን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በመገኘት የ2017 ዓ.ም የ1ኛ ሩብ ዓመት የመልካም አስተዳደር ቅሬታና አቤቱታ አቀራረብና አፈታት ሥራዎች ላይ ድጋፍና ክትትል አድርጓል ::
ቡድኑ በድጋፍና ክትትሉ የተለያዩ በቪዲዩ በፎቶና በወረቀት የተሰነዱ ሰነዶችን የተመለከተ ሲሆን ቢሮው በሩብ ዓመቱ ያከናወነው አፈፃፀም አመርቂ እንደሆነ በመግለፅ ቀጣይ ከመልካም አስተዳደር ቅሬታና አቤቱታ አቀራረብና አፈታት ጋር በተያያዘ ለሌሎች በከተማ አስተዳደሩ ለሚገኙ ቢሮዎች የተሞክሮ ማዕከል እንደሚሆን ተናግረዋል ::
የቢሮ ኃላፊ አማካሪ ወ/ሮ አበበች ነጋሽ የመልካም አስተዳደር እቅድ አፈፃፀም ለመገምገም የመጣውን ቡድን አባላት አመስግነው ድጋፍና ክትትሉ የበለጠ ጠንክረና ለተሻለ ውጤት እንድንሰራ ትልቅ አስተዋፅኦ ያደርጋል ብለዋል ::
የከንቲባ ፅ/ቤት መልካም አስተዳደርና አቤቱታ ዘርፍ ቡድን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በመገኘት ድጋፍና ክትትል አደረገ::
0 Comments