(መስከረም 27/2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ከከንቲባ ፅህፈት ቤት ለመጡ ሱፐርቪዥን አባላት የዝግጅት ምዕራፍ አፈፃፀም ሁኔታውን አስመልክቶ በሩብ ዓመቱ የተከናወኑ ዋናዋና ሥራዎችን አቅርቦ ውይይት ተካሂዷል ::
በከተማ አስተዳደሩ የሚገኙ ቢሮዎችን የዝግጅት ምዕራፍ ስራ ለመገምገም በከተማ ደረጃ ከተመረጡ ቢሮዎች አንዱ ትምህርት ቢሮ መሆኑን የገለፁት የሱፐርቪዥን አባል አቶ አሽናፊ በ2016 ዓ.ም የታየው የተማሪዎች አጠቃላይ ውጤት መሻሻል ለማስቀጠል እንዲቻል በዝግጅት ምዕራፍ ቢሮው እያከናወነ የቆየውን ሥራ ማየት አስፈላጊ መሆኑን አብራርተዋል፡፡ አያይዘውም የ2016 በጀት ዓመት ሥራ አፈፃፀም እንዲሁም የ2017 ዓ.ም እቅድና የዝግጅት ምዕራፍ አፈፃፀም ያለበትን ሁኔታ የሱፐርቪዥን ቡድኑ በ18 ትምህርት ቤቶች ፣ በወረዳና በክፍለ ከተማ ት/ጽ/ቤቶች ላይ ምልከታ እንዳደረገ አብራርተዋል :: በዚህም የተሻለ አፈጻጸም መኖሩን ቡድኑ ለማረጋገጥ መቻሉን ጨምረው አብራርተዋል፡፡
የከንቲባ ፅህፈት ቤት ሱፐርቪዥን ቡድን በአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ በመገኝት የዝግጅት ምዕራፍ አፈፃፀም ላይ ምልከታ አደረገ ::
0 Comments