የእቅድና በጀት ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት የትምህርት ሴክተሩን የ6ወር ስትራቴጂክ እቅድ አፈጻጸም ገመገመ።

by | ዜና

(ታህሳስ 20/2017 ዓ.ም) በግምገማው የክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት የእቅድና በጀት ተጠሪዎችን ጨምሮ የቢሮው የዘርፉ ባለሙያዎች የተሳተፉ ሲሆን በመርሀ ግብሩ የቢሮውና የክፍለ ከተሞች የ2017 ዓ.ም የ6 ወር መሪ እቅድ ተገምግሟል።


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የእቅድና በጀት ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጌታሁን ለማ በ2017 ዓ.ም በስድስት ወራት ውስጥ በቢሮ እና በክፍለ ከተማ ደረጃ በስትራቴጂክ እቅዱ የተቀመጡ የትኩረት መስኮችን መሰረት በማድረግ የተከናወኑ ተግባራት ያሉበትን ደረጃ በመገምገም በቀጣይ የተሻለ ስራ ለመስራት እንዲቻል ታስቦ ውይይቱ መካሄዱን ገልጸዋል።

ዳይሬክተሩ አያይዘውም በስትራቴጂክ እቅዱ የ6 ወር አፈጻጸም ሪፖርት ላይ የሚደረገው ውይይት ቀጥሎ በቀጣይ ከቢሮው የማኔጅመንት አባላት እና ከአጠቃላይ ሰራተኛው ጋር ተካሂዶ ሪፖርቱ ለሚመለከታቸው አካላት የሚላክ መሆኑን አስታውቀዋል።

በግምገማ መርሀ ግብሩ የቢሮው እና የአስራ አንዱ ክፍለ ከተሞች የ2017 ዓ.ም የ6 ወር የስድስት ወር እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል።

0 Comments