የአፋን ኦሮሞ ቋንቋን እንደ ሁለተኛ ቋንቋ ለሚያስተምሩ የግል ትምህርት ቤት መምህራኖች ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቀቀ::

by | ዜና

(የካቲት 1/2017 ዓ.ም) የአፋን ኦሮሞ ቋንቋን እንደ ሁለተኛ ቋንቋ ለሚያስተምሩ የግል ትምህርት ቤት መምህራኖች ሲሰጥ የነበረው ስልጠና የመጨረሻ ዙር ስልጠና ተጠናቀቀ ::

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የመምህራንና ትምህርት አመራር ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ አበራ ቢሮው ከኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ባደረገው ጥናትና ምርምር ውጤት ግኝት መሰረት ስልጠናው መዘጋጀቱ ተናግረዋል ::

ቀደም ሲል ቋንቋውን እንደ ሁለተኛ ቋንቋ የሚያስተምሩ የመንግስት ትምህርት ቤት መምህራን የአቅም ግንባታ ስልጠና ሲካሄድ መቆየቱን ያስታወሱት ዳይሬክተሩ ለግል ትምህርት ቤት መምህራን ስልጠናው መዘጋጀቱ መምህራን በተመሳሳይ አቅም ትምህርቱን መስጠት እንዲችሉና ተመሳሳይ አተገባበር እንዲከተሉ ያደርጋል ብለዋል:: አያይዘውም በቀጣይ በሚደረግ ድጋፍና ክትትል የስልጠናው ውጤት እንደሚመዘንና ተግባራዊነቱ ላይ በትኩረት እንደሚሰራ አብራርተዋል::

ስልጠናው በሁሉም ክፍለከተማ የሚገኙ አፋን ኦሮሞ ቋንቋን እንደሁለተኛ ቋንቋ ለሚያስተምሩ የግል ትምህርት ቤት መምህራን በ3 ዙር ሲሰጥ መቆየቱ የሚታወስ ነው ::

0 Comments