(ህዳር 20/2017 ዓ.ም) በውይይቱ ከቢሮ ጀምሮ እስከ ክፍለከተማ ድረስ የተቋቋሙ የጥናትና ምርምር ኮሚቴ አባላትን ጨምሮ የክፍለከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት የዘርፉ አስተባባሪዎች የተሳተፉ ሲሆን ቼክ ሊስቱ በሁሉም የመንግስት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለሚካሄድ የድጋፍና ከትትል ስራ መዘጋጀቱ ተገልጻል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ትምህርት ጥናትና ምርምር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዮሀንስ ተስፋዬ በትምህርት ተቋማት የሚካሄድ የትናትና ምርምር ስራ በመማር ማስተማር ሂደቱ የሚስተዋሉ ችግሮችን በመቅረፍ የተማሪዎችን ውጤትና ስነ ምግባር ለማሻሻል የሚያስችል ተግባር እንደመሆኑ ቢሮው በየደረጃው ባለው መዋቅር ስራውን የሚመሩ ኮሚቴዎችን አዋቅሮ ወደ ተግባር መግባቱን አስታውቀዋል።
ዳይሬክተሩ አያይዘውም ቢሮው በ2017ዓ.ም ተማሪዎችን በሂሳብና እንግሊዘኛ የትምህርት አይነቶች ውጤታማ ለማድረግ ያዘጋጀው ስትራቴጂ በትምህርት ቤቶች ምንያህል በጥናትና ምርምር ስራ እየተደገፈ እንደሚገኝ በማረጋገጥ በቀጣይ ጥናትና ምርምር ለሚሰሩ መምህራንም ሆነ ባለሙያዎች አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ታስቦ የሚካሄድ የድጋፍና ክትትል ተግባር መሆኑን አመላክተዋል፡፡
ለድጋፍና ክትትሉ በተዘጋጀው ቼክ ሊስት በሁሉም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተግባራዊ የጥናትና ምርምር ኮሚቴ ስለመቋቋሙ እና እቅድ አዘጋጅተው ወደ ተግባር ስለመግባታቸውና ሌሎች ከጥናትና ምርምር ስራዎች ጋር ተያያዥነት ያላቸው ተግባራትን በዝርዝር ማካተቱን የቢሮው የጥናትና ምርምር ባለሙያ አቶ ተስፋጽዮን አይናለም አስገንዝበዋል፡፡
0 Comments