የአጠቃላይ ትምህርት ጥናትና ምርምር ዳይሬክቶሬት ለቢሮው ባለሙያዎች ስልጠና ሰጠ፡፡

by | ዜና

(መስከረም 9/2017 ዓ.ም) ስልጠናው በተግባራዊ ጥናትና ምርምር) (action research ዙሪያ የተሰጠ ሲሆን የኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ የዘርፉ ምሁር ዶክተር ኤፍሬም ስልጠናውን ሰጥተው በተሳታፊዎች የተለያዩ አስተያየቶችና ጥያቄዎች ቀርበው ምላሽ ተሰቱዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ትምህርት ጥናትና ምርምር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዮሃንስ ተስፋዬ በመርሀ ግብሩ ባስተላለፉት መልዕክት የአጠቃላይ ትምህርት ጥናትና ምርምር ዳይሬክቶሬት በቅርቡ የተዋቀረ ስራ ክፍል መሆኑን ጠቁመው የዛሬው መርሀ ግብር የስራ ክፍሉን ተግባር እና ኃላፊነት ከማስተዋወቅ በሻገር በተግባር የተደገፈ የጥናትና ምርምር (Action research) ጽንሰ ሀሳብ ዙሪያ በቂ ግንዛቤ በመፍጠር ውጤታማ የመማር ማስተማር ስራ ለመስራት ታስቦ መዘጋጀቱን አስታውቀዋል፡፡

በተጨማሪም በጥናትና ምርምር የተደገፈ ተግባር ለትምህርት ስራው ውጤታማነት የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን ገልጸው የስልጠናው ተሳታፊዎች የሚያከናውኑትን ተግባር በጥናትና ምርምር ስራ በመደገፍ ተቋሙን ውጤታማ ማድረግ እንደሚገባቸው አመላክተዋል፡፡

0 Comments