የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ ፕሮግራም ለፍትሀዊነት (GEQIP-E) በፕሮግራሙ በተያዘ በጀት ተገዝተው የተሰራጩ ንብረቶችን ለመለየትና ኮድ ለመስጠት በተዘጋጀ ቼክ ሊስት ዙሪያ ኦረንቴሽን ሰጠ።

by | ዜና

(የካቲት 19/2017 ዓ.ም) ቋሚ ንብረቶቹ በፕሮግራሙ በተያዘ በጀት ከ2011 – 2016 ዓ.ም ድረስ ተገዝተው ለትምህርት ተቋማት የተሰራጩ ሲሆን ድጋፍና ክትትሉ ንብረቶቹ ያሉበትን ሁኔታ በመለየት የመለያ ኮድ ለመስጠት ታስቦ እንደሚካሄድ ተገልጿል።

በድጋፍና ክትትሉ በከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ GEQIP-E ፕሮግራም ለትምህርት ተቋማት ተደራሽ የሆኑ ግብአቶች በተለይም ለልዩ ፍላጎት ተማሪዎች አገልግሎት እንዲሰጡ የተሰራጩ ግብአቶች በአግባቡ ተደራሽ ስለመደረጋቸው እንዲሁም ለተማሪዎች አገልግሎት እንዲሰጡ የተዘረጉ የውሀ መስመሮችና ማጠራቀሚያዎች ምን ያህል አገልግሎት ላይ እንደዋሉ ለማረጋገጥ እንደሚካሄድ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ የGEQIP-E የአዲስ አበባ ፕሮግራም ኮርድኔተር አቶ አሸናፊ ገቢሳ አስታውቀዋል።

አቶ አሸናፊ አያይዘውም በፕሮግራሙ በጀት በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ወቅት ተማሪዎች ርቀታቸውን ጠብቀው መማር እንዲችሉ በ10,000,000 ብር ወጪ ተገዝተው በየትምህርት ቤቱ የተሰራጩ መቀመጫዎችና ጠረጴዛዎችን በመለየት የመለያ ኮድ ለመስጠት ታስቦ በድጋፍና ክትትሉ ለሚሳተፉ የቢሮና የክፍለ ከተማ ባለሙያዎች ኦረንቴሽኑ መሰጠቱን አመላክተዋል።

0 Comments