(ጥር 24/2017 ዓ.ም) በመርሀ ግብሩ የክፍለ ከተማ የመረጃ ዝግጅትና አስተዳደር ባለሙያዎችን ጨምሮ ከቢሮው ጉዳዩ የሚመለከታቸው ባለሙያዎች የተሳተፉ ሲሆን ባለሙያዎቹ በቡድን እና በጋራ በመሆን ሞጁሎቹን በመገምገም የተለያዩ የማስተካከያ ሀሳቦችን ለሚመለከታቸው አካላት አቅርበዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ትምህርት መረጃ ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ታዬ ወልደኪዳን በመርሀግብሩ መክፈቻ ባስተላለፉት መልዕክት የአመታዊ የትምህርት መረጃ መጽሄት አዘገጃጀት እና የአጠቃላይ ትምህርት አመላካች ሞጁሎችን ጨምሮ በቢሮው እና በክፍለ ከተማ ደረጃ ለ2016ዓ.ም አመታዊ የትምህርት መጽሄት ጋር በተገናኘ የተዘጋጁ መረጃዎችን የአርትኦት ስራ በመስራት ለህትመት ዝግጁ ማድረግ እንዲቻል ታስቦ መርሀግብሩ መዘጋጀቱን ገልጸው በግምገማው የሚሰጡ የማስተካከያ ሀሳቦችን በማካተት ለቢሮው ማኔጅመንት በማቅረብ ሞጁሎቹን ወደ ተግባር የማስገባት ስራ እንደሚሰራ አመላክተዋል።
ቢሮው በከተማ ደረጃ ካዘጋጀው የ2016ዓ.ም ዓመታዊ የትምህርት መረጃ መጽሄት ባሻገር ለአስራ አንዱ ክፍለ ከተሞችም የ2016ዓ.ም አመታዊ መጽሄት ለማሳተም ቅድመ ዝግጅት ማድረጉን የአጠቃላይ ትምህርት መረጃ ዝግጅትና አስተዳደር ቡድን መሪ አቶ ደስታ አብረሀም ገልጸው በግምገማው በክፍለ ከተማ ደረጃ ለአመታዊ መጽሄቱ የተዘጋጁ መረጃዎችን ኤዲት በማድረግ ለህትመት ዝግጁ የማድረግ ስራ እንደሚሰራ አስታውቀዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአፋን ኦሮሞ አጠቃላይ ትምህርት መረጃ ዝግጅትና አስተዳደር ቡድን መሪ አቶ አዲስ ዘገየ በበኩላቸው ከአመታዊ የትምህርት መረጃ መጽሄት አዘገጃጀት እና ከአጠቃላይ ትምህርት አመላካቾች ጋር በተገናኘ በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጁ ሞጁሎችን በዘርፉ ልምድ ባላቸው ባለሙያዎች ወደ አፋን ኦሮሞ ቋንቋ በማስተርጎም ለህትመት የማዘጋጀት ስራ እንደሚሰራ አስገንዝበዋል።
0 Comments