የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ትምህርት መረጃ ስራ አመራር ቡድን ለክፍለከተማ የመረጃ አስተዳደር ቡድን መሪዎች ስልጠና ሰጠ።

by | ዜና

(ቀን ሚያዚያ 7/ 2016 ዓ.ም) ስልጠናው በዋናነት ቀደም ሲል በየክፍለ ከተማው የተደራጁ የትምህርት መረጃዎችን በማጥራት በአንድ ቋት በማስገባት ለሚፈለገው አገልግሎት ማዋል እንዲቻል ታስቦ መዘጋጀቱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ትምህርት መረጃ ስራ አመራር ቡድን መሪ አቶ ደስታ አብረሀም ገልጸው ስልጠናው መረጃዎቹ ሲደራጁ ያልተካተቱ የትምህርት ተቋማት በድጋሜ ተካተው ተአማኝነቱ የተረጋገጠና ጥራቱን የጠበቀ መረጃ ለባለድርሻ አካል ተደራሽ ለማድረግ የሚያግዝ መሆኑን አስታውቀዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የትምህርት ቴክኖሎጂና መረጃ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ደረጀ ዳኜ በበኩላቸው ዘንድሮ ከቢሮ ጀምሮ እስከ ትምህርት ቤት ድረስ ከመረጃ ማደራጀት ጋር በተገና ኘ በቅንጅት በመሰራቱ ቀደም ሲል ሲስተዋሉ የነበሩ ችግሮች አለመከ ሰታቸውን ጠቁመው ስልጠናው እስካሁን የተሰበሰቡ መረጃዎችን ትክክለኛነት በማረጋገጥ ለሚፈለገው አገልግሎት ለማዋል የሚያግዝ መሆኑንም አስረድተዋል።

በመርሀ ግብሩ የቢሮው የመረጃ አስተዳደር ባለሙያ አቶ አስቻለው አድራሮ ከልዩ ፍላጎት ትምህርት ጋር በተገናኘ መረጃዎች እንዴት መደራጀት እንደሚገባቸው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና  ሰተዋል።

0 Comments

https://twitter.com/aacaebc

SITE VISITORS

  • 0
  • 2
  • 486
  • 1,563
  • 7,525
  • 236,221
  • 236,221