የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የኢንፎርሜሽን ኮሚዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ልማትና ማስፋፋት ዳይሬክቶሬት በ2017 ዓ.ም 1ኛ ሩብ አመት እቅድ አፈጻጸም ላይ ውይይት አደረገ፡፡

by | ዜና

(ጥቅምት 7/2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የኢንፎርሜሽን ኮሚዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ልማትና ማስፋፋት ዳይሬክቶሬት በሁሉም ክፍለ ከተማ ከሚገኙ የትምህርት ቴክኖሎጂና መረጃ ቡድን መሪዎች ጋር በ2017 ዓ.ም 1ኛ ሩብ አመት የእቅድ አፈጻጸም ላይ ውይይት አደረገ ፡፡

የሩብ አመት ሪፖርት በቀረበበት ወቅት የቴክኖሎጂ ቡድን የመሰረተ ልማትና ጥገና ስራዎች ፤ የተማሪዎች ኦንላይን ምዝገባ ፤ እንዲሁም የተማሪ የክፍል ድልደላና የመምህራን መረጃን በቴክኖሎጂ የታገዘ ለማድረግ ሰፊ ስራዎች መሰራታቸው ተጠቅሷል፡፡

የኢንፎርሜሽን ኮሚዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ልማትና ማስፋፋት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ደረጀ ዳኜ በውይይቱ ላይ እንዳሉት የትምህርት ስራን በቴክኖሎጂ ለማገዝ እየተሰራ ያለውን ስራ ዳር ማድረስ የዳይሬክቶሬቱና በሁሉም ክፍለ ከተሞች የሚገኙ ተሳታፊዎች ሓላፊነት እንደሆነ ጠቁመው ፤ የመማር ማስተማር ስራውን ስኬታማ ለማድረግ የመጀመሪያ ምእራፍ ስራዎችን በማጠናቀቅ ሙሉ ለሙሉ ወደትግበራ እንዲገባ አሳስበዋል፡፡

በሩብ አመቱ 563 ትምህርት ቤቶችን ወደ ሲስተም ማስገባት ከተሰሩ ስራዎች ውስጥ አንዱ መሆኑን የጠቆሙት የሶፍትዌርና ሲስተም ልማት አስተዳደር ቡድን መሪ ወ/ሮ ሰላም ተስፋዬ በበኩላቸው የተማሪዎች የክፍል ድልድል ፤ የመምህራንን መረጃ ወደ ሲስተም የማስገባት ፤ የሲስተም ተጠቃሚዎች ሲስተም ፍተሻ (User Acceptance Test) ብሎም የአሰልጣኞች አሰልጣኝ ስልጠና (TOT TEAINING) ቅድመ ዝግጅት መከናወኑን አብራርተዋል፡፡ በቀጣይም የመምህራንን መረጃ በሲስተም የማደራጀትና የማጠናቀቅ ስራዎች እንዲሁም በሌሎች የለርኒንግ ማኔጅመንት ፤ዲጂታል ላይብረሪ፤ ላይብረሪ ማኔጅመንትና የስኩል ፖርታል በትምህርት ቤቶች ወደተግባር የማስገባት ስራ ትኩረት ተሰጥቶት የሚሰሩ ስራዎች እንደሆኑ ተናግረዋል፡፡

በውይይቱ ላይ መሰረተ ልማትና ኢ-ስኩልን አስመልክተው ለተነሱ የግልጽነት ጥያቄዎች በቡድን መሪዎችና ዳይሬክተሩ ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል፡፡

0 Comments