(የካቲት 4/2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ለቢሮ ዳይሬክተሮች በ2017 በጀት ዓመት በ6 ወራት የተከናወኑ የቁልፍ ውጤት አመላካች እቅድ አፈፃፀም ፣ አገልግሎት አሰጣጥ እንዲሁም በሌብነትና ብልሹ አሰራር ላይ ምዘና ያካሄደ ሲሆን ምዘናውን የቢሮው እቅድና በጀት ዳይሬክተር አቶ ጌታሁን ለማ የሪፎርምና አገልግሎት አሰጣጥ ክትትል ድጋፍና ምዘና ዳይሬክተር ተወካይ አቶ ፋንታሁን እያዩና የዳይሬክቶሬቶቹ ባለሙያዎች ተገኝተው ተመልክተዋል፡፡
የቢሮ ሃላፊ አማካሪና የዘርፉ ሃላፊ ወ/ሮ አበበች ነጋሽ ቀደም ሲል በ467 የትምህርት ተቋማት ለ3 ጊዜ በተደረገ ክትትልና ድጋፍ እንዲሁም በተሰጠ ግብረመልስ መሰረት ፍረጃ ተደርጎ ውጤታቸውን እንዲያውቁ የተደረገ መሆኑን ገልጸው ፤ አሁን እየተደረገ ያለው ምዘና በቀጣይ ለሚሰጥ እውቅናና የተሻለ አፈጻጸም ያሳዩ የሥራ ክፍሎችን ቀጣይ የልምድ ልውውጥ ማእከል ለማድረግ የሚያስችል እንደሚሆን ተናግረዋል፡፡ አያይዘውም የ6 ወራት የተማሪ ውጤትን ማእከል ያደረገ ምዘና በትምህርት ቤቶች ወረዳና ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤቶች በቅርብ የሚደረግና ተመሳሳይ ፍረጃ በመስጠት የተሻለ አፈጻጸም ላላቸው እውቅና የሚሰጥ መሆኑን አብራርተዋል፡፡
0 Comments