(ጥር 30 /2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሱፐርቪዥን ዳይሬክቶሬት ለ1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሴት ርእሳነ መምህራንና ሱፐርቫይዘሮች የአመራርነት ሚና ላይ ትኩረት ያደረገ ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እየሰጠ መሆኑ ገልጻል::
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሱፐርቪዥን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጥላዬ ዘውዴ ስልጠናውን በከፈቱበት ወቅት እንዳሉት በትምህርት ሥርዓቱ ውስጥ ያሉ ከፍተኛ ሴት አመራሮችን ማብቃት የትምህርት ሥርዓቱን ማሳደግ መሆኑን በመረዳት የቢሮው ዳይሬክቶሬት ስልጠናውን ማዘጋጀቱን ገልፀው ፤ የስልጠናው ተሳታፊዎች ብቁ ሆነው፤ በያሉበት ተቋም የሚመሯቸውን የተለያየ ጫና ያለባቸውን ሴቶች ማነሳሳትና ማብቃት እንደሚጠበቅባቸው ተናግረዋል::
ዳይሬክተሩ አያይዘውም ስልጠናው የሱፐርቫይዘር መዋቅሩ የሚጠበቅበትን የትምህርት ጥራትና ብቁ ዜጋ የማፍራት ተልእኮ ማሳካት የሚችልበትንና ሴት ሱፐርቫይዘሮች ለትምህርት ስርዓቱ ድጋፍና ክትትል በማድረግ ሂደት ውስጥ ያላቸውን የአመራርነት ሚና ከፍ የሚያደርግ እንደሚሆን ያላቸውን እምነት ተናግረዋል ፡፡
በአመራርነት ደረጃ ያሉ ሴቶች በጎ ተፅእኖ ፈጣሪነት ለማሳደግና ሌሎችን በማብቃት ረገድ ሊኖራቸው ስለሚገባ እውቀት እና በመሪነት ሚናቸው ውስጥ ሊያጋጥሟቸው የሚችሉ እንቅፋቶች ተፅዕኖ ሳያሳድሩባjቸው መወጣት የሚችሉባቸውን ዘዴዎች ስልጠናው በዋናነት ትኩረት የሚያደርግባቸው ነጥቦች መሆናቸው ተመላክቷል::
ስልጠናውን የስፓርክ ቫሊ የሃገር ውስጥ መንግስታዊ ያልሆነ ተቋም ዳይሬክተር በሆኑት ትእግስት ተስፋዬ እየተሰጠ ሲሆን፤ የቢሮው ሱፐርቪዢን ዳይሬክቶሬት ውስጥ ያሉ የሱፐርቪዥን ባለሙያዎች እየተሳተፉ እንደሆነ ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡
0 Comments