(ታህሳስ 19/2017 ዓ.ም) በመድረኩ በ6 ወራት ውስጥ በዘርፉ ስር የሚገኙት መምህራን ልማት ፣ የጥናትና ምርምር እና አጠቃላይ ሱፐርቪዥን ዳይሬክቶሬቶች ሥራ አፈፃፀም ሪፓርት ቀርቦ ግምገማ ተካሄዳል ::
የቢሮው ምክትል ቢሮ ኃላፊና የዘርፉ ሀላፊ አቶ አሊ ከማል የሥራ አፈፃፀም ሪፖርቱ በቀረበበት ወቅት እንዳሉት የስራ ክፍሎቹ በ 2ሩብ ዓመት ያከናወኑትን ተግባር ሪፖርት ለውይይት ማቅረባቸው የተሻሉ አፈፃፀሞችን አጠናክረው ለማስቀጠል እጥረቶችን ደግሞ እቅዳቸውን ከልሰው ለተሻለ ሥራ የሚዘጋጁበትን ግብዓት የሚያገኙበት ይሆናል ብለዋል :: አያይዘውም በሥራችን አመርቂ ውጤት ለማስገኝት በቀጣይ ከሚመለከታቸው ዩንቨርስቲዎች ጋር በጋራ በመሆን የአቅም ማጎልበቻ ስልጠናዎች እናዘጋጃለን ሲሉ ተናግረው። ለትምህርት ጥራትና ለተማሪ ስነምግባርና ውጤት መሻሻልም ትኩረት ተሰጥቶት እንዲሰራ አቅጣጫ ሰጥተዋል ::
በሶስቱ ዳይሬክቶሬቶች ስር የሚገኙ ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎችን ጨምሮ የክፍለ ከተማ ሱፐርቪዥን ክላስተር አስተባባሪዎች ባለሙያዎችና ቡድን መሪዎች ተሳትፈዋል::
0 Comments