(ጥቅምት 6/2017 ዓ.ም) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የትምህርት ግብዓት አቅርቦትና ስርጭት ያለበት ደረጃ ግምገማ የተካሄደ ሲሆን በግምገማው ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ፣ የቢሮ የትምህርት ግብዓት ፍላጎትና አቅርቦት ስርጭት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን መለሰ ፣ የዳሬከቶሬቱ ባለሙያዎች እና የክፍለ ከተማ የትምህርት ቤት መሻሻል ቡድን መሪዎች ተሳትፈዋል፡፡
በግምገማው ላይ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2017 የትምህርት ዘመን የሚሰጠው ትምህርት ውጤታማ እንዲሆን ከግብዓት አቅርቦትና ስርጭት አካያ በተለይም ከተማሪዎች የመማሪያ መጻሕፍት ፣ የዩኒፎርምና የደብተር አቅርቦትና ስርጭት አንጻር ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተካሄዳል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ የ2017 የትምህርት ዘመን ከመጀመሪ በፊት የትምህርት ግብዓት ፍላጎትን መሰረት በማድረግ በርካታ ተግባራት መከናወናቸውንና ስርጭቶች መካሄዳቸውን በመጥቀስ ሲከናወኑ የቆዩ ስራዎች ይበልጥ ተጠናክረው እንዲፈጸሙ በትኩረት መሰራት እንደሚገባ አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡
የትምህርት ግብዓት አቅርቦትና ስርጭት ያለበት ደረጃ ተገመገመ፡፡
0 Comments