የቢሮ ጠቅላላ ካውንስል አባላት የቢሮውን የአጠቃላይ ትምህርት ሱፕርቪዥንን እና የፋይናንስ ዳይሬክቶሬትን የ15 ቀናት እቅድ አፋጻጸም ገመገሙ።

by | ዜና

(ጥር 29/2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ጠቅላላ ካውንስል አባላት የቢሮውን የአጠቃላይ ትምህርት ሱፕርቪዥንን እና የፋይናንስ ዳይሬክቶሬትን የ15 ቀናት እቅድ አፈፃፀምን ከመደበኛ እቅድ አፈጻጸምና ከሪፎርም ስራዎች አተገባባር አካያ ግምገማዉን አካሂዳል።

            

የቢሮ ሀላፊ አማካሪና የዘርፉ ሀላፊ ወ/ሮ አበበች ነጋሽ ጠቅላላ ካውንስሉ የአዲስ አበባ ከተማ የፕብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀይል ልማት ቢሮ አገልግሎት አሰጣጥ ማናል መሰረት በየ15 ቀኑ ውይይቶችንና ግምገማዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ በመግለጽ በዛሬው መድረክ የቢሮው የአጠቃላይ ትምህርት ሱፕርቪዥንን እና የፋይናንስ ዳይሬክቶሬትን የ15 ቀናት እቅድ አፋጻጸም ከመደበኛ እቅድ አፈጻጸምና ከሪፎርም ስራዎች አተገባባር አካያ ለግምገማ መቅረቡን በመጥቀስ በቀጣይ ሁሉም ዳይሬክቶሬቶች በወጣው መርሀ ግብር መሰረት እቅድ አፈጻጸማቸዉን የሚያቀርቡና የሚገመገም መሆኑን ገልጸዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ ሳምሶን መለሰ በበኩላቸው የሚቀርቡ ሪፖርቶች ለሌሎች የመማማሪያ መድረክ እንዲሆን የሚያግዝ እንዲሁም ምን ያህል ተግባራትን እያከናወንን እንደምንገኝ የምናይበትና የተቀራረበ አፈጻጸም እንዲኖር የሚረዳ በመሆኑ ውይይቱ ትኩረት ተሰጥቶት ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ትምህርት ሱፕርቪዥንን እና የፋይናንስ ዳይሬክቶሬትን የ15 ቀናት እቅድ አፋጻጸም ሪፓርት ከመደበኛ እቅድና ከሪፎርም ስራዎች አተገባበር አንጻር በአጠቃላይ ትምህርት ሱፕርቪዥን ዳይሬክተር በሆኑት በአቶ ጥላዬ ዘውዴ እና በፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ቡድን መሪ በሆኑት በአቶ ግሩም አስማረ ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበታል፡፡

0 Comments