የቢሮ ጠቅላላ ካውንስል አባላት የቢሮውን የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ስራዎች የ6 ወራት እቅድ አፋጻጸም ገመገሙ።

by | ዜና

(ጥር 2/2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ጠቅላላ ካውንስል አባላት የቢሮውን የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ስራዎች የ6 ወራት እቅድ አፋጻጸም ከመደበኛ እቅድ አፈጻጸምና ከሪፎርም ስራዎች አተገባባር አካያ ግምገማዉን አካሂዳል።

             

የቢሮ ሀላፊ አማካሪና የዘርፉ ሀላፊ ወ/ሮ አበበች ነጋሽ የአዲስ አበባ ከተማ የፕብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀይል ልማት ቢሮ አገልግሎት አሰጣጥ ማናል መሰረት ጠቅላላ ካውንስሉ በየ15 ቀኑ ውይይቶችንና ግምገማዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ በመግለጽ በዛሬው መድረክ የቢሮው የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ስራዎች የ6 ወራት እቅድ አፋጻጸም ከመደበኛ እቅድ አፈጻጸምና ከሪፎርም ስራዎች አተገባባር አካያ ለግምገማ መቅረቡን በመጥቀስ በቀጣይ ሁሉም ዳይሬክቶሬቶች በወጣው መርሀ ግብር መሰረት እቅድ አፈጻጸማቸዉን የሚያቀርቡና የሚገመገም መሆኑን ገልጸዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የህዝብ ግንኙነትና የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ አበበ ቸርነት የዳይሬክቶሬቱን የ6 ወራት እቅድ አፈጻጸም ከመደበኛ እቅድና ከሪፎርም ስራዎች አተገባበር አንጻር በማቅረብ ውይይት ተካሂዶበታል፡፡

የቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊና የቢሮ ሀላፊ ተወካይ የሆኑት አቶ አሊ ከማል መድረኩ ስራዎች ውጤታማ እንዲሆኑና አንዱ ክፍል ያለዉን መልካም አፈጻጸም በማቅረብ ሌሎች የስራ ክፍሎች ወስደው እንዲያሰፉት የመማማሪያ መድረክ በመሆን ያገለግላል ብለዋል፡፡

0 Comments