የሰኞ ማለዳ የሰራተኞች የዕውቀት ሽግግር መርሀ ግብር ለተቋሙ ራዕይ ተልዕኮና እሴቶች መሳካት አቅም በመሆን እያገዘ እንደሚገኝ ተገለጸ፡፡

by | ዜና

(ጥቅምት 25/2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የሰኞ ማለዳ ከስራ ሰዓት መግቢያ በፊት የሚያዘጋጀው የሰራተኞች የዕውቀት ሽግግር መርሀ ግብር የ2017 የትምህርት ዘመን የ1ኛ ሩብ አመት የእውቀት ሽግግር እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በዛሬው ዕለት የተገመገመ ሲሆን በመድረኩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ፣ የቢሮ ማኔጅመንት አባላትና ሰራተኞች ተሳታፊ ሆነዋል።

በመርሀ ግብሩ ላይ የሪፎርምና አገልግሎት አሰጣጥ ክትትል ድጋፍና ምዘና ቡድን መሪ አቶ ሀፍቱ ብርሀኑ የ2017 የትምህርት ዘመን የ1ኛ ሩብ አመት የእውቀት ሽግግር መርሀ ግብርን እቅድ አፈጻጸም ሪፖርትን አቅርበው ውይይት የተካሄደ ሲሆን በመድረኩ ማጠቃለያ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ የዕውቀት ሽግግር መድረኩ የተቋሙን ራዕይ ተልዕኮና እሴቶች ለማሳካት አቅም በመሆን እያገለገለ እንደሚገኝ ጠቅሰው በመድረኩ ላይ እውቀታቸዉን ለማካፈል የሚፈልጉ ሰራተኞች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱ መላክም መሆኑን በመግለጽ ሰራተኛው በቀጣይ መድረኩን በመጠቀም ለሌሎች የማካፍላቸው እውቀቶች አሉኝ ብሎ ካመነ መድረኩ ክፍት መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ሀላፊው አክለዉም የእውቀት ሽግግር መድረኩ ከቢሮ ጀምሮ በመዋቅሩ እስከ ትምህርት ቤት ድረስ ተጠናክሮ እንዲቀጥል በትኩረት እየተሰራ መሆን ተናግረዋል፡፡

0 Comments